fbpx
Saturday, May 25, 2024
Amharicበአራቱም እግሮቻቸው በመጓዝ ሳይንቲስቶችን ግራ ያጋቡት የኡላስ ቤተሰብ

በአራቱም እግሮቻቸው በመጓዝ ሳይንቲስቶችን ግራ ያጋቡት የኡላስ ቤተሰብ

በቱርክ የሚኖሩት እኜ ቤተሰብ፤ በሁለት እግራቸው ከመራመድ ይልቅ በእጃቸው መዳፍ መሬትን በመያዝ እንደ እንስሳ ”ዳዴ” ማለትን ከጀመሩ ሰንብቷል።የሰው ልጅን የዝግመተ ለውጥ እሳቤዎችን የሚፈታተን ተግባር ነው ሲሉ ሳይንቲስቶችን ግራ በተጋባ መንፈስ ስለ ሁኔታው ለጋዜጠኞች ሃሳባቸውን አካፍለዋል።

የኡላስ ቤተሰብ የእጃቸውን መዳፍ በመጠቀም በ 2006 “በአራት እግሮች የሚራመድ ቤተሰብ” በሚል ርዕስ በቀረበው የቢቢሲ ዘጋቢ ፊልም ላይ ታይተዋል።

በለንደን የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት የዝግመተ ለውጥ ሳይኮሎጂስት የሆኑት ፕሮፌሰር ኒኮላስ ሃምፍሬይ ከቤተሰቡ 18 ልጆች መካከል ስድስቱ በሰው ልጆች ላይ ከዚህ ቀደም የማይታይ ባህሪ እያሳዩ ነው ብለዋል። ከዚህ ጋራም በተያያዘ በሚያሳዝን ሁኔታ ከነዚህ ስድስቱ አንዱ ከዚህ አለም በሞት መለየቱም ተገልጿል።

ሃምፍሬይ በዚህ አስደናቂ ቤተሰብ ላይ ባደረገው ጥናት ሁነኛ መገረማቸውን በ‘60 ደቂቃ አውስትራሊያ’ ላይ ተናግሯል፡- “ሳይንሳዊ ልብወለድ ውስጥ እንኳን የሰው ልጆች ወደ እንስሳት ሁኔታ ይመለሳሉ ብዬ ጠብቄ አላውቅም ነበር” ብላል።

አክሎም “ከሌላው የእንስሳት ዓለም የሚለየን በሁለት እግሮች የምንራመድ እና ጭንቅላታችንን በአየር ላይ የምንይዝ ዝርያዎች መሆናችን ነው። እርግጥ ነው፣ ቋንቋ መጠቀማችንም ከእንስሳቱ ከሚለዩን ነገሮች አንድ ነው። እነዚህ ሰዎች ያንን ድንበር ያልፋሉ።” ብሏል።

ዘጋቢ ፊልሙ የኡላስ ቤተሰብን “በሰው እና በዝንጀሮ መካከል ያለው ግንኙነት ኩልል አድርጉ የሚሳይ” ሲል ገልጿል። ሦስት ሚሊዮን ዓመታትን የፈጀው የዝግመተ ለውጥ ወደ ኃላ በመመለስ ኢ-ዝግመተ-ለውጥ ሊፈጠር እንደሚችል ዘጋቢ ፊልሙ አስነብቧል።

ምንም እንኳን ሃምፍሬይ ይህን ፅንሰ-ሀሳብ “ጥልቅ ስድብ” ብቻ ሳይሆን “በሳይንሳዊም ኃላፊነት የጎደለው” ነው ሲል በጥብቅ ተችቷል። ዘጋቢ ፊልሙ እነዚህ ልጆች “መኖር የለባቸውም” ሲልም አሰምቷል።

የሊቨርፑል ዩንቨርስቲ ተመራማሪዎች ከቤተሰቡ የተወጣጡ ልጆች ላይ ባደረጉት ጥናት ከሰዎች ይልቅ ከዝንጀሮ ጋር ተመሳሳይነት ያለው አፅም እንዳላቸው አረጋግጠዋል። እንዲሁም የተጨማደደ ሴሬብልም ቢኖራቸውም ይህ ገን እነሱን እንደ ሰው ቀጥ ብለው እንዳይራመዱ የሚያደርግ እንዳልሆነ በጥናታቸው ማወቅ ችለዋል። በተጨማሪም ቤተሰቡ ጉልበታቸውን ከሚጠቀሙ ዝንጀሮዎች በተቃራኒ፣ ለመራመድ የእጃቸው መዳፍ እንደሚጠቀሙ ተገልጿል።

ሃምፍሬይ ቤተሰቡ በዝንጀሮዎችና በሰዎች መካከል ያለውን የዝግመተ-ለውጥ ሂደት ልዩነት ሊያሳይ እንደሚችል ጠቁሟል፡- “በዚህ ቤተሰብ ውስጥ እየተመለከትን ያለነው ነገር እንደ ቺምፓንዚዎች መራመድ ካቆምንበት ጊዜ ጋር የሚመጣጠን ሳይሆን የሰው ዘር ዛፍ ላይ ከመኖር ተላቁ ሙሉ በሙሉ በሁለት እግሩ ቆሞ መራመድ እስከጀመረብት ወቅት ደረስ ያለ የዝግመተ-ለውጥ ሂደት አካል ነው ብዬ አስባለሁ” ብላል።

በተጨማሪም በቤተሰቡ ውስጥ ያሉ ህጻናት ከ9 ወር ዕድሜያቸው በኋላ እንዲቆሙ ሳያበረታቱ በመቅረታቸው ዕድገታቸው ሊገታ እንደሚችል ገምቷል። ይሁን እንጂ አሁን ላይ ልጆቹ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ለመርዳት ፊዚዮቴራፒና ልዩ መሣሪያዎችን ጨምሮ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ተገልጿል።

ሃምፍሬይ እድገታቸውን ለማየት ወደ ቱርክ በተመለሰበት ወቅት ልጆቹ በእንቅስቃሴያቸው ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዳደረጉ አስተውሏል። የልጆቹ በቶሎ ማገገም፤ የሰው ልጅ አካል ምን ያህል ውስብስብና ለሁኔታዎች በፍጥነት የሚገራ መሆኑን የሚያሳዩ ነው ተብሏል።

NATO, wire
In a move aimed at bolstering defenses against potential threats, six NATO countries bordering Russia announce plans to build a ‘drone wall’. Led by...
debate
A deep dive into the Swedish legal system's ongoing debate concerning the use of anonymous witnesses in court proceedings, discussing the potential implications on...
roof
A person unexpectedly fell from a significant height into a store in central Uppsala, causing astonishment among locals. The circumstances surrounding this extraordinary event...
police
In a significant first, France has held a war crimes trial concerning the Syrian Civil War, sentencing three high-ranking Syrian intelligence officials to life...
addict
A report reveals that 20% of all premature deaths in Sweden are associated with alcohol, tobacco, or narcotics use. The study paints a broader...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here
Captcha verification failed!
CAPTCHA user score failed. Please contact us!

Most Popular

የሕዝብ ቁጥር የማሽቆልቆል ቀውስ? ሳይንሳዊ ጥናቶች በቅርቡ በጣም ጥቂት ሰዎች ምድር ላይ እንደሚቀሩ አሳዩ

በዕለት ተዕለት ወሬዎቻችን ላይ አከራካሪ እየሆነ የመጣው ''ህዝብ ቁጥር መጨመር፤ ተጨማሪ ችግሮች ያመጣል?'' ወይስ ''የህዝብ ቁጥር መቀነስ ነው ሊያሳስበ የሚገባው?'' የሚለው ጥያቄ የብዙሃንን ትኩረት ስቧል። አብዛህኛው ሃሳብ፣ በተለይ ከምዕራባዊያን የሚሰማው፤ ሰዎች መብዛታቸው የወደፊት ሕይወታችን አደጋ ላይ እንደሚጥል ነው። በእዚሁ ሃገራችንም የኑሮ ውድነትን ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር የሚያገናኙ ’ባለ-ቀለሞች’ እየተበራከቱ መተዋል። ግን እውነተኛው፤ በሳይንስ የተደገፈው ነገር ተቃራኒ መሆኑ ከሰሞኑን ተሰምቷል።

በአራቱም እግሮቻቸው በመጓዝ ሳይንቲስቶችን ግራ ያጋቡት የኡላስ ቤተሰብ

በቱርክ የሚኖሩት እኜ ቤተሰብ፤ በሁለት እግራቸው ከመራመድ ይልቅ በእጃቸው መዳፍ መሬትን በመያዝ እንደ እንስሳ ”ዳዴ” ማለትን ከጀመሩ ሰንብቷል።የሰው ልጅን የዝግመተ ለውጥ እሳቤዎችን የሚፈታተን ተግባር...

የዲላን አስደናቂ ጉዞ: ሐኪሞቹን ያስደመመው ልጅ

ማንኛውም ትንሽ ልጅ በካንሰር ሲሰቃይ ማየትም፤ መስማትም በጣም አሳዛኝ ነው።ዲላን  ግን ብዙዎችን በሚያበረታታ ሁኔታ በጥንካሬ ተዋግቶታል። እንደ እድል ሆኖ በበሽታ ምክኒያት አይትርፉም የተባሉ ልጆች፤ በሂይወት...