የሚያምር ነጭ ጥርስ እንዲኖረን ሁላችንም የምንፈልገው ነገር ነው። ጥሩ የጥርስ ንጽሕናን መጠበቅ በራስ የመተማመን ስሜትን ለማጎልበትና የፊታችንን መልክ ለማሻሻል ይረዳል ።እርግጥ ነው ፣ የጥርስ ሐኪምን እርዳታ ማግኘት ለአብዛኛዎቻችን ውድ ነው። በተጨማሪም አንዳንዶቻችን ጥርሳችንን በተገቢው መንገድ ለመንከባከብ ጊዜ መመደብ ችላ የምንልበት ነገር ነው።
የጥርስ ልማም(በድድና በጥርስ መጋጠሚያ ላይ ያለው ቆሻሻ)፣ ዋናው መንስኤ መጥፎ የአፍ ንጽሕና ነው። በየቀኑ ጥርሶቻችንን መፋቅ በዘላቂነት የጥርስ ልማምን ለማጥፍት ሁነኛ መፍትሄ ነው። በተጨማሪ ከዚህ በታች ያሉትን የራስ የሕክምና ዘዴዎች በየዕለቱ መጠቀም የጥርስ ቆሻሻን ከማስወገድ ባሻገር ትናንሽ ቆሻሻዎች በጥርሶቻችን ላይ እንዳይጠራቀሙ ይረዱናል።
በአፋችን ውስጥ በማይክሮ ደረጃ ምን እየተከናወነ እንዳለ ማሰብ በየቀኑ የምናደርገው ነገር አይደለም ፤ ጥርሶቻችንን ሙሉ ለሙሉ መርሳት የድድ በሽታ ፣ የጥርስ መበላሸት እና የከፋ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ግን ማስታወስ ጠቃሚ ነው።
ከዚህ በታች ቤት ውስጥ የጥርስ ልማምን ለማስወገድ ልታደርጋቸው የምትችላቸውን አሥር ነገሮች ዘርዝረናል።
- 1 – ቤኪንግ ሶዳ
ቤኪንግ ሶዳ ጥርስን ለማጽዳት ይረዳል። በተጨማሪ በአንድ ጊዜ ነጭ ያደርጋቸዋል።
- 2 – ሃይድሮጅን በፔርኦክሳይድ
ሃይድሮጅን ፐርኦክሳይድ የተባለው ጠቃሚ ፀረ ተሕዋስያን ጥርሶን ሊያነጻ ይችላል። ለጥቂት ወራት (በቀን አንድ ጊዜ) ያለማቋረጥ መጠቀም የጥርስዎን ነጭነት ለማሻሻል ጥሩ መንገድ ሲሆን ፥ የመጥፎ የአፍ ጠረንንም ያስወግዳል።
- 3 – ፖም
የተፈጥሮ የጥርስ ሳሙና! ፖም መብላት ጥርስህን ለማጽዳት እንዲሁም መጥፎ የአፍ ጠረንን ለመዋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይችላል።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጭጋግ ያለው የፖም ቅርፊት ሌሎች የምግብ ፍርስራሾችን ከጥርስህ ላይ በማስወገድ ቆሻሻን ይጠርጋል ።
- 4 – ብርቱካን
በቫይታሚን ሲ የበለጸጉ ብርቱካን በአጠቃላዩ የአፍ ንጽሕና ለመጠበቅ ጠቃሚ ነው። ብርቱካን በአፍህ ውስጥ የሚራቡ ባክቴሪያዎችን ለመዋጋት ጥሩ ናቸው ።
- 5 – ቤኪንግ ሶዳ እና አልዎ ቪራ
አዎ፣ አልዎ ቪራ መራራ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በሚያስደንቅ ሁኔታ የጥርስ ልማምን የማስወገድ አቅም አለው። አንድ የሻይ ማንኪያ አልኦ ቬራ ፣ አራት የሻይ ማንኪያ ግሊሰሪን ፣ 5 የሻይ ማንኪያ የቤኪንግ ሶዳ ፣ የሎሚ ዘይት እና ውሃ በማድረግ ይቀላቅሉ እና ጥርሶዎን ይፋቁበት። ለልማም አስገራሚ ፍቱን ነው።
- 6 – በቫይታሚን ሲ የበለፀጉ ምግቦች
እንደ ቲማቲምና እንጆሪ ያሉት ምግቦች፤ ባክቴሪያዎችን ከአፍ የማስወገድ አቅም ባላቸውን ፀረ ተሕዋስያን የበለጸጉ ናቸው።የቲማቲሞችን እና እንጆሪ ፍሬዎችን በማውጣት እና በጥርሶ ላይ መቀባት (ከዛ ለአምስት ደቂቃዎች መተው) አፍዎን ከባክቴሪያ ነፃ ለማድረግ ጥሩ መንገድ ነው (ይህን በሳምንት ሁለት ጊዜ ያድርጉ)።
- 7 – ቅመም የበዛባቸው ምግቦች
ቅመም የበዛባቸው ምግቦች በአፍዎ ውስጥ ብዙ ምራቅ እንዲፈጠር ስለሚያደርጉ ጥርስንና ድድን ለማጽዳት ይረዳሉ ።
- 8 – ፀረ-ልማም የጥርስ ሳሙና
የኮኮናት ዘይት ፣ የቤኪንግ ሶዳ ፣ የስርቪያ ዱቄት እና የወይራ ዘይት በመቀላቀል የአፍን ልማም ለመበተን በጣም ጠቃሚ የሆነ የተፈጥሮ የጥርስ ሳሙና በቤት ውስጥ ልታዘጋጁ ትችላላቹ ።
- 9 – ካሮት
ሁላችንም ካሮት በጨለማ ውስጥ ለማየት እንደሚረዳን በአፈ ታሪክ እናውቃለን። ነገር ግን ስንቶቻችን ነን ጥርስንም እንደሚያጠነክር የምናቀው?
የአይን ጥራትን ለማሻሻል እንደሚያግዙን ሁሉ፣ በካራቲን እና ቫይታሚን ኤ የበለጸጉት የካሮት ዝርያዎች የጥርስ ልማምን ያስወግዳሉ።
- 10 – የአልሞንድ ፍሬዎች
አልሞንድ ከአፍዎ ላይ የልማም ንጣፎችን ለማስወገድ በጣም ጥሩ ናቸው። ሻካራ ልጣጭ ስላላቸው በጥርሳችን ላይ ተሰንቅሮ የቀሩትን ቆሻሻዎች ለማስወገድ ይረዱና።