fbpx
Saturday, May 25, 2024
Amharicየአስፕሪን ጥቅም እና ጎንዮሽ ጉዳቶች

የአስፕሪን ጥቅም እና ጎንዮሽ ጉዳቶች

በቀን አንድ አስፕሪን መውሰድ ከጥቅሙ የበለጠ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ጥናቶች አመላከቱ፡፡

በቅርቡ በአሜሪካ ብቻ በተደረጉ ጥናቶች ከ40 ዓመት በላይ የሆናቸው ከአምስት ሰዎች መካከል አንዱ በየቀኑ አስፕሪን ተጠቃሚ መሆን አመላክተዋል። ምንም እንኳን ዶክተሮች የልብ ድካምን ወይም ስትሮክን ለመከላከል በየቀኑ ዝቅተኛ የአስፕሪን መጠን እንዲወሰድ የሚመክሩ ቢሆንም፣ ብቅ ካሉ ማስረጃዎች ግን ሊያስከትሉ የሚችሉትን አንዳንድ አደጋዎች ላይ በማተኮር መድኃኒቱ ለሁሉም አዋቂዎች እንዳይመከር አድርጎታል።

በዓለም ላይ የሞት መንስኤ የሆኑት የልብ እና የደም ሥር ሕመም ታሪክ ላላቸው ታካሚዎች ለብዙ አሥርተ ዓመታት አስፕሪንን በዋነኛነት ዶክተሮች ሲያዙ ነበር። ሆኖም አስፕሪን የልብ ድካም ለመከላከል ወሳኝ የመከላከያ መስመር ሆኖ ይቆያል፡፡ ነገር ግን ባለፈው ዓመት የዩኤስ የመከላከያ አገልግሎት ግብረ ኃይል ሁለት ትላልቅ ክሊኒካዊ ጥናቶች ከ 60 እስከ 69 ዓመት ለሆኑ ሰዎች አስፕሪን ያለው ጥቅም የበለጠ እንደሆነ ያሳዩ ቢሆንም በተመሳሳይ ሰአት ለበሽታ የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ መሆኑንም አሳውቀዋል፡፡  አሁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መድሃኒቱን መጠቀማቸውን ቀጥለዋል። ብዙዎቹ ያለ ሐኪም ምክር መድሃኒቱን መውሰድ የጀመሩ ሲሆን ይህም በአንጎል እና በአንጀት ውስጥ የደም መፍሰስ አደጋ ላይ ሊያስከትል እንደሚችል ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ሌሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች እየወሰዱትም አይደለም። 

አስፕሪን የልብ ድካምን እንዴት ይከላከላል? 

በ 1900ዎቹ መጀመሪያ ላይ ካርዲዮሎጂስት ላውረንስ ክራቨን አስፕሪን የሚወስዱ ታካሚዎቻቸው አነስተኛ የልብ ድካም እንዳላቸው አስተውለዋል፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ, በርካታ ክሊኒካዊ ጥናቶች በቀን አስፕሪን መውሰድ የልብ ድካምን የማስወገድ አቅም እንዳለው ይስማሙበታል። በ1989 የተደረገ አስደናቂ ጥናት የልብ ህመም ወይም የስትሮክ ህመም ታሪክ በሌላቸው 22,000 ሃኪሞች አስፕሪን እንዲወስዱ በማድረግ 44 በመቶ የቀነሰ የልብ ህመም አሳይተዋል። በመደበኛነት አሴቲልሳሊሲሊክ አሲድ ተብሎ የሚጠራው አስፕሪን፤ ፕሌትሌትስ የሚባሉት ህዋሶች አንድ ላይ ሆነው እንዳይረጉ ይከላከላል። የልብ ሕመም ባለባቸው ታማሚዎች ፕሌትሌቶች ባልተለመደ ሁኔታ ይከማቻሉ፣ ኦክስጅንን ወደ ቲሹዎች በማቋረጥ የልብ ድካም ወይም ስትሮክን  ያስከትላሉ፡፡ ሆኖም አስፕሪን ደሙን ቀጭን ያደርገዋል፤ ፕሌትሌትሶች ደግሞ መርጋትን የሚፈጠሩ ሴሎችን እንዳይጣበቁ ያደርጋሉ። ይህ የሆነበት ምክንያት መድሀኒቱ በፕሌትሌቶች ላይ የተቀመጠውን ሳይክሎኦክሲጅኔዝ የተባለውን ኢንዛይም በመዝጋት ፕሮስጋንዲን የተባሉ ሆርሞን መሰል ሞለኪውሎችን በጉዳት ጊዜ ፕሌትሌቶች እንዳይሰበሰቡ ስለሚያደርግ ነው። የአስፕሪን ደም የማቅጠን ባህሪያቶቹ እንዳሉ ሆኖ፤ ተጠቃሚዎቹ ከፍተኛ የደም መፍሰስ እድላቸውን ከፍተኛ ያደርገዋል። የደም መፍሰስ አደጋ ሊገጥማቸው የሚችሉ ታካሚዎች መድሃኒቱን መውሰድ እንደሌለባቸው ባለሙያዎች ይስማማሉ፤ እንዲሁም ታካሚዎች እድሜያቸው እየገፋ በሄደ ቁጥር የደም መፍሰስ አደጋንም ይጨምራል። 

አስፕሪንን ማን ነው መጠቀም ያለበት? 

ዕድሜያቸው ከ40 እስከ 59 ዓመት ለሆኑ ሰዎች፣ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ አገልግሎት ግብረ ኃይል ለልብ ድካም አደጋ ተጋላጭነት ያለው ማንኛውም ሰው በየቀኑ አስፕሪን ሲጀምር አደጋዎቹን እና ጥቅሙን ለመገምገም ከሐኪሞቻቸው ጋር እንዲማከሩ ይናገራል። ነገር ግን ከ 60 አመት በኋላ ያሉ ታካሚዎች፤ ግብረ ኃይሉ አስፕሪንን እንደ ዋና የመከላከያ እርምጃዎች እንዳይወስዱ ይመክራል፡፡ ግብረ ኃይሉ የውሳኔ ሃሳቦቹን በ2022 የለወጠው በሁለት ትላልቅ ጥናቶች ሲሆን፤ መድሃኒቱ ለልብ ድካም እንዲሁም ለስትሮክ የመጋለጥ እድልን ቢቀንስም፤ እንደ የአንጎል ደም መፍሰስ እና በአንጀት ውስጥ ደም መፍሰስን የመሳሰሉ ለከባድ የደም መፍሰስ ችግር የመጋለጥ እድላቸውን ከፍ ያደርገዋል። 

የአስፕሪን ጉዳቶችን እና ጥቅሞቹን እንዴት ይመዝናሉ? 

በብዛት አደጋዎችን እና ጥቅሞችን ማመዛዘን ቀላል አይደለም፡፡ በስታንፎርድ የሕክምና ትምህርት ቤት ፕሮፌሰር የሆኑት ራንዳል ስታፎርድ “ተጨማሪ አሻሚ ሃሳቦች ባሉበት መካከል አንድ ዓይነት ሃሳብ ያለው ቡድን መኖሩ የማይቀር ነው” ብለዋል። ከ60 በላይ ለሆኑ ስትሮክ ወይም የልብ ድካም ላላጋጠማቸው ሰዎች ነገር ግን ለወደፊት ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው ሰዎች፣ “አስፕሪን መውሰድ ሊኖርባቸው ይችላል።” በተጨማሪም በዚህ ቡድን ውስጥ በትክክል ማን እንዳለ ለመወሰን ተጨማሪ ምርምር ያስፈልጋል፣ በማለትም ገጸዋል።  አዲሶቹ ጥናቶች አስፕሪን ከ60 ዓመት በላይ ለሆኑ አዋቂ ሰዎች የተጣራ ጥቅም እንዳለው በማሳየት የአስርት አመታትን መረጃዎች ይቃረናሉ። የቴክሳስ የልብ ኢንስቲትዩት ፕሬዝዳንት እንዲሁም የቤይለር የህክምና ኮሌጅ የህክምና ፕሮፌሰር የሆኑት ኤድዋርዶ ሄርናንዴዝ ይህ ሊሆን የቻለው ሌሎች የመከላከያ እርምጃዎች አሁን ስላሉም እንደሆነ ገልጸዋል። 

የአስፕሪን የጎነዮሽ ጉዳቶች 

አስፕሪን የኮሎሬክታል ካንሰርን እንደሚከላከል ቢታወቅም አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት መድሃኒቱ ለሌሎች ካንሰሮች ተጋላጭነትን ይጨምራል። 

መፍትሄው? 

የዩኤስ የመከላከያ አገልግሎቶች ግብረ ኃይል ምክሮች ቀደም ሲል ላሉት ዝቅተኛ መጠን ያለው አስፕሪን የሚወስዱ ታካሚዎች ማቆምን አይመለከቱም፤ እንዲሁም መድኃኒቱን ተጠቃሚ የነበሩ ነገር ግን ማቋረጥ የሚፈልጉ ሕመምተኞች ከሐኪሞቻቸው ጋር በቅድሚያ መነጋገር እንዳለባቸው አጥብቀው ይመክራሉ። አንዳንድ የልብና የደም ሥር ሕመም ያለባቸው ሰዎች አስፕሪን ለመውሰድ ሲያስቡ ከሐኪማቸው ጋር እንዲማከሩ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ነገር ግን ጥናቶች እንደሚያሳዩት እንደ አሜሪካ ያሉ ከፍተኛ ገቢ ባላቸው አገሮች በግምት 35 በመቶ የሚሆኑት አስፕሪን ተጠቃሚ ግለሰቦች ይህን አያደርጉም። ዞሮ ዞሮ የጤና ባለሙያዎች የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች በታካሚው ውጤት ላይ ትልቅ ተፅእኖ እንዳላቸው ይናገራሉ። የልብ ድካምን ለመከላከል ተስፋ የሚያደርጉ፤ ጤናማ ምግቦችን መመገብ እና አዘውትረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ አለባቸው “ይህ የበለጠ ዋጋ ያለው ወይም ከአስፕሪን ህክምና የበለጠ ዋጋ ያለው ነው” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።

NATO, wire
In a move aimed at bolstering defenses against potential threats, six NATO countries bordering Russia announce plans to build a ‘drone wall’. Led by...
debate
A deep dive into the Swedish legal system's ongoing debate concerning the use of anonymous witnesses in court proceedings, discussing the potential implications on...
roof
A person unexpectedly fell from a significant height into a store in central Uppsala, causing astonishment among locals. The circumstances surrounding this extraordinary event...
police
In a significant first, France has held a war crimes trial concerning the Syrian Civil War, sentencing three high-ranking Syrian intelligence officials to life...
addict
A report reveals that 20% of all premature deaths in Sweden are associated with alcohol, tobacco, or narcotics use. The study paints a broader...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here
Captcha verification failed!
CAPTCHA user score failed. Please contact us!

Most Popular

የሕዝብ ቁጥር የማሽቆልቆል ቀውስ? ሳይንሳዊ ጥናቶች በቅርቡ በጣም ጥቂት ሰዎች ምድር ላይ እንደሚቀሩ አሳዩ

በዕለት ተዕለት ወሬዎቻችን ላይ አከራካሪ እየሆነ የመጣው ''ህዝብ ቁጥር መጨመር፤ ተጨማሪ ችግሮች ያመጣል?'' ወይስ ''የህዝብ ቁጥር መቀነስ ነው ሊያሳስበ የሚገባው?'' የሚለው ጥያቄ የብዙሃንን ትኩረት ስቧል። አብዛህኛው ሃሳብ፣ በተለይ ከምዕራባዊያን የሚሰማው፤ ሰዎች መብዛታቸው የወደፊት ሕይወታችን አደጋ ላይ እንደሚጥል ነው። በእዚሁ ሃገራችንም የኑሮ ውድነትን ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር የሚያገናኙ ’ባለ-ቀለሞች’ እየተበራከቱ መተዋል። ግን እውነተኛው፤ በሳይንስ የተደገፈው ነገር ተቃራኒ መሆኑ ከሰሞኑን ተሰምቷል።

በአራቱም እግሮቻቸው በመጓዝ ሳይንቲስቶችን ግራ ያጋቡት የኡላስ ቤተሰብ

በቱርክ የሚኖሩት እኜ ቤተሰብ፤ በሁለት እግራቸው ከመራመድ ይልቅ በእጃቸው መዳፍ መሬትን በመያዝ እንደ እንስሳ ”ዳዴ” ማለትን ከጀመሩ ሰንብቷል።የሰው ልጅን የዝግመተ ለውጥ እሳቤዎችን የሚፈታተን ተግባር...

የዲላን አስደናቂ ጉዞ: ሐኪሞቹን ያስደመመው ልጅ

ማንኛውም ትንሽ ልጅ በካንሰር ሲሰቃይ ማየትም፤ መስማትም በጣም አሳዛኝ ነው።ዲላን  ግን ብዙዎችን በሚያበረታታ ሁኔታ በጥንካሬ ተዋግቶታል። እንደ እድል ሆኖ በበሽታ ምክኒያት አይትርፉም የተባሉ ልጆች፤ በሂይወት...