fbpx
Wednesday, February 5, 2025
Amharicየዲላን አስደናቂ ጉዞ: ሐኪሞቹን ያስደመመው ልጅ

የዲላን አስደናቂ ጉዞ: ሐኪሞቹን ያስደመመው ልጅ

ማንኛውም ትንሽ ልጅ በካንሰር ሲሰቃይ ማየትም፤ መስማትም በጣም አሳዛኝ ነው።ዲላን  ግን ብዙዎችን በሚያበረታታ ሁኔታ በጥንካሬ ተዋግቶታል።

እንደ እድል ሆኖ በበሽታ ምክኒያት አይትርፉም የተባሉ ልጆች፤ በሂይወት ሲጸኑ መመለከት የሚያንጹ ነው።

ዲላን ሊትል ከዘጠኝ አመታት በፊት ሲወለድ፤ ዶክተሮች ልጁ ላይ አንድ ልክ ያልሆነ ሁኔታ እንዳለ ተገነዘቡ። በጀርባው ላይ ያለው ቆዳ ጠቆር ያለ ሲሆን የተቀረው የሰውነቱ ክፍል ደግሞ በልደት ምልክቶች(በተለምዶ ማርያም የሰጠችው ምልክት ተብሎ የሚጠራው) ተሸፍኗል።

ከተወለደ በኋላ ዲላን ወዲያውኑ ወደ የሕጻናት የፅኑ እንክብካቤ ክፍል (Neonatal Intensive Care Unit) ተወሰደ። በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ብዙም ሳይቆይ ትንሹ ልጅ Congenital Melanocytic Nevus በተባለ ከባድ ህመም እየተሰቃየ እንደሆነ ግልጽ ሆነ።  80 በመቶው የሚሆነው የዲላን ደካማ አካላት በልደት ምልክቶች ተሸፍኗል።

እናቱ ካራ፣ በአትላንታ፣ ጆርጂያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሆና የምትሰራ ሲትሆን፤የምትወደውን ልጇን በዚህ ሁኔታ ስትመለከት በጣም ደነገጠች። በእርግዝና ወቅት, ጽንሱ ምንም አይነት ችግር እንዳለበት የሚጠቁም ነገር አልነበረም። ሁሉም አልትራሳውንድ እና ምርመራዎች የሚያሳዩት ይህን ነበር።

ሆኖም ካራ ልጇን ለመጀመሪያ ጊዜ ስትመለከት፣ ከጠበቀችም ውጭ ሆነባት።

ዲላን በተወለደ ጊዜ ጀርባው ሙሉ በሙሉ ጥቁር ነበር። ፊቱ፣ እጆቹ እና እግሮቹ ሁሉም በልደት ምልክት ተሸፍነው ነበር። ከጆሮው በላይ እስከ ታች ድረስ እንዲሁም በትከሻው ፣ በሆዱ እና በጠቅላላው ጀርባው ላይ የሚታየው እየው ጥቁር የልደት ምልክት ነው።

አምስት ሳምንታት ሲሆነው ዲላን ሜላኖማ(melanoma) የተባለ በሽታ እንዳለው ለማወቅ የ PET እና ኤምአርአይ  ስካን ተደረገለት።ዲላን በአንጎሉ ውስጥ ብዙ የሜላኒን ኢጢዎች ክምችት ነበረበት።

ትንሹ ልጅ 4 ወራት ሲሞላው በአእምሮው ውስጥ ባሉ ሜላኒን ምክንያት አዙሪት ይይዘው ጀመረ። ዶክተሮች ለወላጆቹ ካራ እና ኒኪ፥ ዲላን በህይወቱ የመጀመሪያ አመታት ውስጥ ብዙ ቀዶ ጥገናዎችን ማድረግ እንዳለበት አስረዷቸው።

በCongenital Melanocytic Nevus የሚሠቃዩ ታካሚዎች በቆዳ ካንሰር የመያዝ እድላቸው ከፍተኛ ነው። ስለዚህ የዲላንን የልደት ምልክቶች በጥንቃቀ መከታተል እጅግ አስፈላጊ ነው።

አብዛኛውን የዲላንን ጀርባ የሸፈነው የልደት ምልክት፤ በጣም ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ ዶክተሮች በቀዶ ሕክምና ሊያስወግዱት ፈለጉ። ነገር ግን ከሌሎች የሕፃኑ የሰውነት ክፍሎች ቆዳን አንስቶ መትከል ስለሚያስፈልገው ቀዶ ጥገናው ቀላል አይሆንም።

ዲላን እያደገ ሲሄድ ዶክተሮቹ በልጁ ላይ ውስብስብ ቀዶ ጥገናዎችን ለማድረግ ወሰኑ። ለ ንቅለ-ተከላው የሚሆን በቂ ቆዳ ለማምረት ዶክተሮች በሰው ሰራሽ መንገድ በቂ የቆዳ ሴሎችን ለመፍጥር ኢንፕላንት በልጁ አካል ውስጥ መትከል ነበረባቸው።

ዲላን ኢንፕላንቱን ለሦስት ወራት በሰውነቱ ውስጥ ተሸክሞ ለቀዶ ጥገናው የሚሆን ተጨማሪ ቆዳ አከማቸ።

ከ26 ቀዶ ጥገናዎች በኋላ፣ የልጁ ግዙፍ የልደት ምልክቶች ግማሽ ያህሉ መወገድ ቻሉ።

እናቱ ካራ ለቴሌግራፍ እንደተናገረችው “ልጄ በየሶስት ወር ቀዶ ጥገና ነበረው።የልደት ምልክቶቹ በድጋሚ እንደማይመለሱበት እና ካንሰር እንደማይሆኑ ተስፋ እናደርጋለን ፣ ግን በማንኛውም ጊዜ ወደ ካንሰር ሊቀየሩ ይችላሉ”።

ምንም እንኳ በርካታ ቀዶ ሕክምና ቢደረግለትም፤ አሳማሚ የማገገሚያ ጊዜያትን ቢያሳልፍም፤ ዲላን ሁሌም ደስተኛ ልጅ ነው።

ካራ ለቴሌግራፍ “ዲላን እጅግ ይገርመኛል፣ ሁል ጊዜ ፊቱ ላይ ፈገግታ ነው የሚታየው። ነርሶች ሁሉ ይወዱታል” ብላ ነበር።

ዲላን ከአብዛኛዎቹ ልጆች የተለየ መልክ እንዳለው ጠንቅቆ ያውቃል። ብዙ ጊዜ ሰዎች መንገድ ላይ ቆም ብለው ያዩታል። ይህ ዲላንን ምንም ቅር አያሰኘወም።

በአጠቃላይ ሰዎች ለእሱ ወዳጆች ናቸው። ነገር ግን አንዳንድ ህጻናት በቆዳው ምክኔያት ያበሽቁትና ይሰድቡት ነበር። ቢሆንም ካራ  ከሰው አይን ልጇን ለመደበቅ አስባ አታውቅም።

“እኔ እሱን ወደ ውጭ ለማውጣት በፍጹም አላፍርም። እንዲጨነቅ ወይም ሊያፍርበት የሚገባ ነገር እንዳለበት እንዲያስብ አልፈልግም” ስትል ገልጻለች።

የዲላን ወላጆች የዲላንን የሕይወት ተሞክሮ እና ጥንካሬ ለሌሎች ለማካፈል የፌስቡክ ገጽ ከፈቱ። ካራ ስለ ዲላን ሁኔታ የበለጠ ግንዛቤ ለመፍጠር ጠንክራ እየሰራች ነው። በልጁ ጠንካራ አስተሳሳብ የተደመሙ በርካታ ሰዎች የዲላን አድናቂዎች ሆኑ።

ስለ ዲላን የወደፊት እጣ ፋንታ ማውቅ ባይቻልም፣ ስለሱ አንድ ነገር ማለት ግን የሚከብድ አይደለም። ዲላን እቺ አለም የሰጠችውን መራር እጣ ፋንታ በመዋጥ፤ ስለ ራሱ የሕይወት በራሱ ብዕር እየጻፈ ያለ ልጅ ነው። ምናልባትም፣ እኛም ይህንን ከሱ መማር ይኖርብን ይሆናል።

speech
Salwan Momika and Salwan Najem are slated to face charges of incitement to racial hatred in January, in a pivotal court case involving desecration...
little girl
An article about the devastating attack on the International Committee of the Red Cross in Donetsk, Ukraine, which resulted in the loss of three...
missile
An account of a Russian missile striking a Ukrainian grain ship in the Black Sea, stirring geopolitical tension and raising concerns over international maritime...
motor
An intense motorcycle crash in Stockholm's Södermalm district led to a city-wide discussion on road safety. The incident, which ended with the motorcyclist being...
teenager
Two teenagers, suspected of plotting a murder, have been arrested in Malmö. The unsettling incident raises questions about youth crime, societal influences, and the...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here
Captcha verification failed!
CAPTCHA user score failed. Please contact us!

Most Popular

የሕዝብ ቁጥር የማሽቆልቆል ቀውስ? ሳይንሳዊ ጥናቶች በቅርቡ በጣም ጥቂት ሰዎች ምድር ላይ እንደሚቀሩ አሳዩ

በዕለት ተዕለት ወሬዎቻችን ላይ አከራካሪ እየሆነ የመጣው ''ህዝብ ቁጥር መጨመር፤ ተጨማሪ ችግሮች ያመጣል?'' ወይስ ''የህዝብ ቁጥር መቀነስ ነው ሊያሳስበ የሚገባው?'' የሚለው ጥያቄ የብዙሃንን ትኩረት ስቧል። አብዛህኛው ሃሳብ፣ በተለይ ከምዕራባዊያን የሚሰማው፤ ሰዎች መብዛታቸው የወደፊት ሕይወታችን አደጋ ላይ እንደሚጥል ነው። በእዚሁ ሃገራችንም የኑሮ ውድነትን ከህዝብ ቁጥር መጨመር ጋር የሚያገናኙ ’ባለ-ቀለሞች’ እየተበራከቱ መተዋል። ግን እውነተኛው፤ በሳይንስ የተደገፈው ነገር ተቃራኒ መሆኑ ከሰሞኑን ተሰምቷል።

በአራቱም እግሮቻቸው በመጓዝ ሳይንቲስቶችን ግራ ያጋቡት የኡላስ ቤተሰብ

በቱርክ የሚኖሩት እኜ ቤተሰብ፤ በሁለት እግራቸው ከመራመድ ይልቅ በእጃቸው መዳፍ መሬትን በመያዝ እንደ እንስሳ ”ዳዴ” ማለትን ከጀመሩ ሰንብቷል።የሰው ልጅን የዝግመተ ለውጥ እሳቤዎችን የሚፈታተን ተግባር...

ሃተታ ዘርአ ያዕቆብ: ለኢትዮጵያ ጊዜያዊ ችግሮች ፍልስፍናዊ መፍትሕ

በታሪክ ትውፊቶች የከበረችው ሃገራችን ኢትዮጵያ፤ ወቅታዊ ችግሮች ፣ የፖለቲካ አለመረጋጋቶች ፣ ጎሳዊ አስተሳሰቦች እና ተያይዞ የሚመጡት አለመግባባቶች እና ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ስጋቶች በእጅጉ የተስፋፉ ይገኛሉ። ሆኖም...