fbpx
Saturday, May 18, 2024
Amharicየአዲስ አበባ የመንግስት ሠራተኞች የብቃት ምዘና: እውነተኛ ተሐድሶ ወይስ ሌላ የፖለቲካ ጫወታ?

የአዲስ አበባ የመንግስት ሠራተኞች የብቃት ምዘና: እውነተኛ ተሐድሶ ወይስ ሌላ የፖለቲካ ጫወታ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት ለሰራተኞቹ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናን ማጠናቀቁን ኢቢሲ ዘግቧል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በአስተዳደሩ በኩል ያለውን አገልግሎት አሰጣጥና ውስጣዊ አሠራር ይበልጥ ለማሳደግ እንዲሁም ለሥራ ተነሳሽነትና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት ታቅዶ የተካሄደ መሆኑ ተዘግቧል።

በመሪህ ረገድ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናው አስተዳደሩ አስተዳደራዊ ተሃድሶን ለመፍጠር የሚያስችለው ትክክለኛ እርምጃ ነው። በአስተዳደር ውስጥ የሚያጋጥሙትን የማያቋርጡ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን ሁለገብ በሆነ መንገድ ለመፍታት መዘጋጀቱን ያመለክታል ። አንካ ሚዲያ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ አስተዳደራዊ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድርሻ ከፍተኛ መሆንን ስትዘግብ ከርማለች። በዚህም ረገድ የአስተዳደሩ እንቅስቃሴ ሊበረታታ ይገባል።

ነገር ግን ይህ እንቅስቃሴ ከብዙ አቅጣጫዎች ሲታይ እውነተኛ ተሐድሶ እያየን ነው ወይስ ሌላ የአስተዳደሩን የፖለቲካ ጫዋታ እየተመለከትን ነው? የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም። ለምሳሌ የግምገማ መስፈርቱን በተመለከተ ግልጽ አለመሆን ፣ ስለ ሂደቱ ግልፅነት ትክክለኛ ጥያቄዎችን ያስነሳል። ግቡ የሚደነቅ ቢሆንም እውነተኛ አስተዳደራዊ ለውጥ ከምንም በላይ ግልጽነትን ይጠይቃል ። አስተዳደሩ በህዝቡ ዘንዳ አመኔታን ለማስፈን አስቦ የነደፈው ይህ እንቅስቃሴ ሳይታወቅ እንዳይሸረሸረው ጥንቃቄ መደረግ ያለበት መሆኑ ግልጽ ነው።

የብቃት ማረጋገጫ ፈተናው ከ15,000 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች መውሰዳቸውን ዘገባው አስፍሯል፤ ይህም አዋጭነቱ በትንሽ ያልተሞከረ አሰራር፣ ሳይሳካ ከቀረ ሊያስከትል የሚችለው የገንዘብ ብክነት የሚካድ አይደለም። አስተዳደሩ ያሉትን የሰው ሃይል ክህሎት ለማሻሻል ያደረገው ልባዊ ጥረት ሳይሆን ከጥራት ይልቅ ቁጥር ላይ ያለውን ትኩረት የሚያሳይ እንዳይሆን ያሰጋል።

የከንቲባው ቢሮ ከብቃት ማረጋገጫውም ባሻገር  ቴክኖሎጂ መር አገልግሎቶችን ለመስጠት እየተዘጋጀ ሲሆን ፣ የገንዘብ ብክነትንና እንግልትን እንደሚያስቀር ቃል ገብቷል ። የአገልግሎት ብቃቱን ለማሻሻልም የተመረጡ የአስተዳደሩን ተግዳሮቶች ለሶስተኛ ወገን በመስጠት ቀልጣፋ እና ተደራሽ ግልጋሎትን ለመዘርጋት ማቀዱን አስታውቋል። ይህ ሁሉ የእንቅስቃሴ ዕቅድ በወረቀት ላይ ጥሩ ድምጽ ያለው ቢሆንም ሁለት ስለት ያለው ሰይፍ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። የሲቪል አገልግሎቶችን ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ  የሥራ ደህንነት ላይ እና የአገልግሎት ተጠያቂነት ላይ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖ ሊጠና የሚገባ ነው።

የዚህ ሁሉ ለውጦች የመጨረሻ ግብ ሌብነት እና ብልሹ አሰራሮችን ለመዋጋት መሆኑ የሚደነቅ ነው። ይሁን እንጂ ሌቦቹ ራሳቸው የደገሱት እና መንስኤውን ለይቶ በቀዶ ጥገና ከማከም ይልቅ እኚን የተለመዱ ቃላቶችን በሚዲያ በመወርወር እድሜን የማራዘም ታክቲክ አለመሆኑን በውጤት ማሳየት አስፈላጊ ነው።

Swedish Liberals Demand Action Against Anonymous Political Campaigning

Friedrich Becker
politics
The Swedish Liberal Party's leader, Johan Pehrson, calls for stricter regulations on anonymous political campaigning. Amidst allegations leveled against Sweden Democrats' disguised social media...

Sweden’s ‘Troll Factories’: A Digital Pandemonium Unmasked

Isla Bennett
mask
The article unpacks an expose by Kalla Fakta, revealing a network of anonymous accounts allegedly affiliated with Sweden Democrats (SD). These accounts disseminate divisive...

Card Payment Glitches in Swedish Grocery Stores

Friedrich Becker
card payment
Several grocery stores in Sweden are facing technical issues with their card payment systems, particularly the 'blipp' or contactless payment method. Despite the glitch,...

Storm in Swedish Politics Over Anonymous Social Media Accounts

Isla Bennett
Sweden
A major conflict ensues in the Swedish politics as the controversy over the use of anonymous social media accounts by the Sweden Democrats to...

Finnair Resumes Flights to Tartu Overcoming GPS Disruptions

Friedrich Becker
Airport
Finnair resumes flights to Tartu in Estonia, overcoming GPS disruptions with innovative, ground-based radio navigation solutions. This stride demonstrates the ongoing resilience and innate...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here
Captcha verification failed!
CAPTCHA user score failed. Please contact us!

Most Popular

የዲላን አስደናቂ ጉዞ: ሐኪሞቹን ያስደመመው ልጅ

ማንኛውም ትንሽ ልጅ በካንሰር ሲሰቃይ ማየትም፤ መስማትም በጣም አሳዛኝ ነው።ዲላን  ግን ብዙዎችን በሚያበረታታ ሁኔታ በጥንካሬ ተዋግቶታል። እንደ እድል ሆኖ በበሽታ ምክኒያት አይትርፉም የተባሉ ልጆች፤ በሂይወት...

በአራቱም እግሮቻቸው በመጓዝ ሳይንቲስቶችን ግራ ያጋቡት የኡላስ ቤተሰብ

በቱርክ የሚኖሩት እኜ ቤተሰብ፤ በሁለት እግራቸው ከመራመድ ይልቅ በእጃቸው መዳፍ መሬትን በመያዝ እንደ እንስሳ ”ዳዴ” ማለትን ከጀመሩ ሰንብቷል።የሰው ልጅን የዝግመተ ለውጥ እሳቤዎችን የሚፈታተን ተግባር...

የጥርስ ሐኪም ሳያስፈልግዎ በቤትህ ውስጥ በምታገኟቸው ነገሮች ጥርሶዎን ነጭ ማድረግ እንዴት ይቻላል?

የሚያምር ነጭ ጥርስ እንዲኖረን ሁላችንም የምንፈልገው ነገር ነው። ጥሩ የጥርስ ንጽሕናን መጠበቅ በራስ የመተማመን ስሜትን ለማጎልበትና የፊታችንን መልክ ለማሻሻል ይረዳል ።እርግጥ ነው ፣ የጥርስ ሐኪምን እርዳታ ማግኘት ለአብዛኛዎቻችን ውድ ነው። በተጨማሪም አንዳንዶቻችን ጥርሳችንን በተገቢው መንገድ ለመንከባከብ ጊዜ መመደብ ችላ የምንልበት ነገር ነው።