ኢትዮጵያ የባህር በር ለመዘርጋት በቅርቡ ከሶማሊላንድ ጋር ስምምነት በጠ/ሚ አብይ በኩል አድርጋለች። ይህ ስምምነት አዳዲስ የንግድ መስመሮችን መክፈትና ወደ ውጭ የሚላኩ ዕድሎችን ማስፋት የሚያስችል ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ አቅም አለው። ይህ ጽሑፍ የባህሩ በር የሚያስገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በመዳሰስ በአካባቢያዊ ግንኙነት ፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ፣ በባሕር ላይ ደህንነት እንዲሁም በዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ለውጦችን ያብራራል ።
የኢትዮጵያ የመሬት አቀማመጥ የሃገር ውስጥ ምርቶችን ለዓለም ገበያ በጥራት ለማቅረብ እንዳይችል ካደረገ ቆይቷል ። ይሁን እንጂ ከሶማሊያ ጋር የተደረገው ስምምነት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ንግድን ለማሳለጥ የባሕር በር እንዲኖራት በማድረግ ለችግሩ መፍትሄ ይሰጣል ። ይህም የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ገቢ ለማሳደግ ፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
በሱማሊያ የወደብ ግንባታና ሥራ ከፍተኛ የመሠረተ ልማት አቅርቦት ያስፈልገዋል። ይህም የመጓጓዣ አውታሮች ፣ የሎጂስቲክስና የድጋፍ አውታሮች እንዲፈጠሩና የተቀላጠፈ አሠራር እንዲኖር ያደርጋል ። ኢትዮጵያ በዚህ ረድፍ ልምድ የሌላት በመሆኑ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ድንበር ዘለል የሎጀስቲክስ አጠቃቀም ፣ የገንዘብ አጠቃቀምና ድንበር ላይ የሚያጋጥሙ ተፈታታኝ ሁኔታዎች በጥንቃቄ ሃላፊነቱን መወጣት ይኖርበታል። ይሁን እንጂ እነዚህ መሰናክሎች በመሠረተ ልማት ዘርፍ ለሚደረገው የአገር ውስጥና የዓለም አቀፍ ትብብር ልዩ ዕድል ይፈጥራሉ ። እንደ አንካ ሚዲያ መላምት እንደ ራሺያ፣ ቻይና፣ የተባበሩት አራብ ኢማራት ያሉ የብሬክስ አገራት በዚህ ዘርፍ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገንዘብ፣ የእውቀት እና የልምድ እርዳታ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
የዚህ ስምምነት አውንታዊ ጥቅም ለሱማሌላንድም ጭምር ነው። አካባቢው በባሕር ላይ ደኅንነት እጦት የሚታወቅ ነው። ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድና ከሌሎችም አጋር አካላት ጋር በመሆን የባህር በርን ለመጠበቅና ያልተቋረጠ የንግድ ፍሰትን ለማረጋገጥ ስር ነቀል የፀጥታ እርምጃዎችን መተግበር ይኖርባታል ። ደህንነትን ለማስጠበቅ የባህር ኃይል ፣ የደኀንነት መጋራት እና የባህር ላይ ጉዞዎች ትብብር ወሳኝ ይሆናል።
በሶማሌላንድ የባሕር በር መዘርጋት በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ለሚኖረው ግንኙነት እጅግ ሰፊ ትርጉም አለው ። ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሳደግና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደት ለመፍጠር ያላትን አከባቢያዊ አቅም ያመለክታል። የዚህ ስምምነት መገለጽ ከ ኢትዮጵያ የብሬክስ አገራትን ከመቀላቀል ጋር አብሮ መሆኑ ደግሞ የስምምነቱ ጉልህ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ አንድምታን ያሳያል። ኢትዮጵያ በሰላማዊ ድርድር የባህር በርን ማስጠበቅ መቻሏ ዲፕሎማሲያዊ ጥንካሬዋን እና ቀጠናዊ ትብብርን እንደምትፈልግ የሚያሳይ ነው ። በተጨማሪም ስምምነቱ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረክ ያላትን አቋም ያጠናክራል ።
የምዕራቡ ዓለም ሚዲያ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት በተመለከተ ያሰራጨው የመጀመሪያው አሉታዊ መግለጫ በዚህ ስምምነት ላይ ተጽዕኖ የማሳደር የምዕራቡን አለም ፍላጎት ያሳየ ነበር። የአፍሪካን ጉዳይ በተመለከተ ትክክለኛና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ሽፋን መስጠት የአፍሪካን ወኪል ፣ ችግሮችን የመቋቋም አቅምና ገለልተኛ ውሳኔ የማድረግ አቅም ማጎልበቱ ተገቢ ነው ።
የኢትዮጵያ-ሶማሊላንድ የባሕር በር ስምምነት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ፣ ቀጣናዊ ትስስርና ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች የጎላ ተስፋ ይዟል ። ኢትዮጵያ ይህን ስምምነት በተሳካ ሁኔታ ማስተናገዷ፤ በሃገሪቷ ላለፉት አመታተ የነበረው የፖለቲካ አለመረጋጋት የምስራቅ አፍሪካን የልማት አጀንዳ በመምራት ረገድ ያላትን አቅም በተመለከተ የነበራውን ጥርጣሬ ዳግም ማስቀረት ትችላለች ። አሁን የትኩረት አቅጣጫው ሁሉን አቀፍ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ማረጋገጥ ፣ የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ውጤታማ መሆን እና የስምምነቱ ኢኮኖሚያዊ አቅም ከፍ እንዲል ከቀጠናው ሃገራት እና ከዓለም አቀፍ አጋር አካላት ጋር ዘላቂ ትብብር ማድረግ መሆን ይኖርበታል ።