fbpx
Friday, November 8, 2024
Politicsየሱዳን የስልጣን ሽኩቻ፡ የተኩስ አቁም ለምን አልተሳካም?

የሱዳን የስልጣን ሽኩቻ፡ የተኩስ አቁም ለምን አልተሳካም?

የሰሜን ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ተቀናቃኝ የጦር አንጃዎችን በሚመሩት ሁለት ጄኔራሎች መካከል በሚካሔደው ውጊያ ተጥለቅልቃለች ። ከስድስት ሚልዮን የሚበልጡ ሰዎች ሸሽተው የነበረ ቢሆንም ሌሎች ደግሞ በጦርነት ቀጣናዎች ውስጥ ለመኖር እየታገሉ ነው ።

እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 15 በዋና ከተማ ካርቱም እና በሀገሪቱ ዙሪያ ባሉ ሁለት ተቀናቃኝ ወታደራዊ ቡድኖች መካከል የተቀሰቀእ ውጊያ, በሱዳን ኦምዱርማን የተፈጠረ ጭስ። ክሬዲት…መሀመድ ኑረልዲን አብደላህ/ሮይተርስ

ሁለቱ ተቀናቃኝ ጄኔራሎች 46 ሚልዮን ሰዎችን የሚኖራባትን ሃገር የግላቸው ጦርነት መናኸሪያ ሲያደርጓት፣ ህዝቦቻቸው ላይ እየደረሰ ያለው ከባድ ጉዳት የሚያሳስባቸው አይመስልም።

ዋና ከተማዋ ካርቱም ሚያዝያ 15 ቀን በተጀመረው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት ደርሶባታል ። የጦር አውሮፕላኖች ባለፉ ቁጥር በፎቅ ጣሪያ ላይ የሚርመሰመሱ ተዋጊዎች እንዲሁም ሕንፃዎችን የሚያሠቃዩ የጦር አውሮፕላኖች በከተማዋ ላይ ተሰራጭተዋል ። የኤሌክትሪክ ኃይል እንደ ልብ አይታይም ፣ የምግብ እጥረትም በከፍተኛ ሁኔታ የተፈጠረ ሲሆን አስገድዶ የመድፈር ፣ የዘረፋ ወንጀሎችም እየተፈጸሙ እንዳሉ መረጃዎች ያሳያሉ።

ሌላው የግጭቱ ዋና ነጥብ በስተ ምዕራብ የሚገኘው የዳርፉር ግዛት ነው ፤ ዳርፉር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ባለፉት አስርተአመታት በ የዘር ማጥፋት ጥቃት ጋር ተያይዞ ስሙ ይጠራል። በዚህ አከባቢ ንጹሃን ታርደዋል ፣ የዕርዳታ ሠፈሮች ተቃጥለዋል፣ እንዲሁም ከቀድሞ አመፅ የሸሹ ስደተኞች ወደ አገራቸው ዳግመኛ ላለመመለስ በወደ ጎሮቤት ሃገር ቻድ ተሰደዋል።

በአርምድ ኮንፍሊክት ሎኬሽን እና ኢቨንት ዳታ ፕሮጀክት መረጃ መሰረት በህዳር ወር ብቻ የጦር ጉዳተኞች  ከ10,400 በላይ እንደሚሆኑ አሳውቋል ።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ መረጃ መሰረት ደግሞ እንደ ግብፅ ፣ ቻድ ፣ ደቡብ ሱዳን እና ማእከላዊው አፍሪካ ሪፐብሊክ ያሉ ጎረቤት አገሮች እንዲሁም በሱዳን ውስጥ ሰላም ወደ አለበት አስተማማኝ ወደሆኑ ቦታዎች አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መሰደዳቸውን አመላክቷል ።

ሁለቱ ጄኔራሎች የበላይነት ለማግኘት በሚያደርጉት ሽኩቻ ፣ በተፎካከሩት የጦር ሠራዊትና ራፒድ ድጋፍ ሰጭ ኃይሎች ተብሎ በሚታወቀው ወራሪ ቡድን መካከል የተፈጠረው ግጭት አገሪቱን በከፍተኛ ፍጥነት ተቆጣጥሯል ።

በብጥብጥ በቆየች ቁጥር፤ በአፍሪካ በህዝብ ብዛት በሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ሱዳን፤ ቀን አልፎላት ወደፊት በሲቪል አገዛዝ ሥር የመሆኗ ተስፋ እየተመናመና ነው።

የትግሉ ሁኔታ ምን ይመስላል?

የአየር ጦር ሃይልን የተቆጣጠረው ጋንታ የሱዳንን ፖርት ጨምሮ አብዛኛውን የሀገሪቱን ክፍል ተቆጣጥሮታል ። ነገር ግን የራፒድ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች ዋና ከተማዋን ካርቱምንና የኦምዱርማንን እና የባህሪን ከተሞች ለመቆጣጠር እየተዋጉ ነው ።ቡድኑም በዳርፉር ግዛት ያለውን ወታደራዊ ይዞታ እስከ ኅዳር መጀመሪያ ድረስ በምዕራብ ዳርፉርና በደቡብ ዳርፉር ግዛቶች የሚገኙትን የጦር ይዞታዎች በመቆጣጠር የሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ የሆነውን ኤል ፋሸርን ለመቆጣጠር ወታደሮችን በማሰባሰብ የተጠናከረ ውጊያ አካሂዷል ።

ዩ.ኤን.ኤን እንደዘገበው በሐምሌ ወር በምዕራብ ዳርፉር በምትገኝ ኤል ጂኔና በተባለች ከተማ ቢያንስ 87 ሰዎች ተገድለው የሞቱበት የጅምላ መቃብር ተገኘተዋል። እንዲሁም በመስከረም ወር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቢያንስ 13 የሚሆኑ የጅምላ መቃብሮችን በተመለከተ አሳማኝ ሪፖርቶች እንደደረሰው ገልጿል ።

በሳኡዲ አረቢያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል በጅዳ ከተማ የተደረገ በሁለቱም ተፋላሚ ወገኖች የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሷል። በዚህም ምክኒያት ተፋላሚዎቹ ለተጎዱ ማህበረሰቦች ሰብአዊ እርዳታ እንዲያደርጉላቸው ያቀረቡት ጥያቄ  እስካሁን ድረስ በአብዛኛው አልተሳካም።

በጥቅምት ወር መገባደጃ ላይ ሁለቱም ወገኖች በሳውዲ አረቢያ ፣ በዩናይትድ ስቴትስና በምሥራቅ አፍሪካ የልማት መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) አባል በሆኑት ሃገራት እንዲሁም ሱዳንን ጨምሮ የስምንት አገሮች አባል መሪዎች ስብሰባው ላይ ተካፍለዋል። ሆኖም ሁለቱ ወገኖች በሰብዓዊ ዕርዳታ ንቅናቄው እገዛ ለማድረግ ቃል ቢገቡም ንግግሩ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ሳያሳካ ቀርቷል ።

ተቀናቃኞቹ ጄኔራሎች እነማን ናቸው?

ዋና ፀሐፊ ፖምፔዮ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ጀነራል ፋታህ አል ቡርሃን። ክሬዲት…ዊኪ ሚዲያ

የጦር አዛዡ ጀነራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ የሱዳን የሞግዚት መሪ ናቸው። ጀነራሉ ወደ ስልጣን የመጡትም ለሶስት አስርት አመታት የሱዳን መሪ በነበሩት ኦማር ሀሰን አልበሽር ላይ ከተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በኋላ በሚያዝያ ወር 2011 ከስልጣን በወረዱበት ወቅት ነበር።

ከዚያ በፊት ጀኔራል አል ቡርሃን በዳርፉር የክልል የጦር አዛዥ የነበሩ ሲሆን፣ ከ2003 እስከ 2008 በተደረጉ ውጊያዎች 300,000 ሰዎች ሲገደሉ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሌሎች ደግሞ ተፈናቅለዋል። ይህ ጦርነት ዓለም አቀፍ አሉታዊ እውቅናን እና በፈጸሙት የሰብዓዊ መብት ረገጣ ሳቢያም ዓለም አቀፍ ውግዘት አስከትሎባቸዋል ።

ሞሐመድ ሀምዳን ዳግሎ (በተለምዶ ሐምድቲ እየተባለ የሚጠራው)።ክሬዲት…ዊኪ ሚዲያ

የጄኔራል አል ቡርሃን ዋነኛ ተቀናቃኝ ሌተናል ጀነራል ሞሃመድ ሃምዳን ሲሆን የሀገሪቱ ራፒድ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች  የወታደራዊ ቡድን መሪ ናቸው ።

በትሑት አመጣጥ ረገድ ሄሜቲ በመባል የሚታወቁት ጄኔራል ሐምዳን በዳርፉር ለተከሰተው ግጭት የከፋ ጥፋት ተጠያቂው የጃንጃዌ ሚሊሺያ ኃይሎች አዛዥ በመሆን ከፍተኛ ዝና አትርፈዋል ።

በጥቅምት 2021 ጄኔራል አል ቡርሃን እና ጄኔራል ሃምዳን በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ስልጣን ለመያዝ በመተጋገዝ የሱዳን መሪ እና ምክትል መሪ እንዲሆኑ አስችሏቸዋል። ይሁን እንጂ ብዙም ሳይቆይ እርስ በእርስ ተጋጭተዋል።

ከዩናይትድ ስቴትስ የመጡትን ጨምሮ በርካታ ዲፕሎማቶች በሁለቱ ጄኔራሎች መካከል የተፈረመውን ስምምነት ለመደራደር ሞክረዋል ፤ ይህ ስምምነት ለሲቪሎች ኃይል ሲሰጣቸው ለማየት ያስችላል ። ይሁን እንጂ ወዲያው የራፒድ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች ወደ ጦር ሠራዊቱ እንደሚገቡ ሊስማሙ አልቻሉም ። ለበርካታ ወራት ውጥረት ሲነግስ ከቆየ በኋላ በሚያዝያ ወር ወታደሮቻቸው እርስ በርስ ለመፋለም ጦርነት አካሄዱ ።

ለምንድነው ሌሎች አገሮች በግጭቱ ውስጥ ጣልቃ እየገቡ ያሉት?

ሱዳን በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ከፍተኛ ቦታን ትይዛለች ። ይህ የባሕር ወሽመጥ በቀይ ባሕር ላይ የሚገኝ ትልቅ የባሕር ዳርቻ ያለው ሲሆን በዓለም ላይ የመርከብ ጉዞው በፍጥነት ከሚካሄድባቸው መንገዶች አንዱ ነው ። ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክ ፣ ቻድ ፣ ግብጽ ፣ ኤርትራ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ሊቢያና ደቡብ ሱዳን ከሰባት አገሮች ጋር የሚያዋስናቸው ድንበሮች ሲሆኑ ብዙዎቹም የሃገሪቷ አለመረጋጋት ስጋት ላይ ጥሏቸዋል።

ብጥብጡ ወደ ዳርፉር ከመዛመቱ በፊጥ፤ዳርፉር ወደ ውጊያው ሊገቡ የሚችሉ የበርካታ አማፂ ቡድኖች መኖሪያ የነበረ ሲሆን የሩሲያ  የግል ወታደራዊ ኩባንያ ዋግነር በዚህ ስፍራ ላይ መቀመጫ አግኝቷል ። ዋግነር ከሱዳንን መንግሥት ጋር በመሆን ብዙ ገንዘብ የሚያስገኝ የወርቅ ማዕድን ሥራ እየሰራ ይገኛል። ራሺያም የጦር መርከቦቿ በሱዳን የቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ እንዲቆዩ ለማድረግም ጥረት እያደረገች ነው።

በተጨማሪም የዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ በጎረቤት ሃገር ቻድ በሚገኝ የአየር ማረፊያ በኩል የጦር መሣሪያዎችን በድብቅ እያቀረበችና የሕክምና አገልግሎት እየሰጠች እንደሆነ የዩናይትድ ስቴትስ ፣ የአውሮፓና የበርካታ የአፍሪካ አገሮች ባለሥልጣናት ገልጸዋል ። ኢመሬትስ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከሰብአዊነት አንጻር ብቻ በማለትም ወቀሳውን አጣጥለዋል።

Ggbet Najlepszy Dostawca Zakładów Online Na Activity I E-sportGgbet Polska Oficjalna Strona Ggbet Zakłady Sportowe My Partner And I Kasyno OnlineContentZakłady Na Esport GgbetZdobądź...
Dallas Mavericks Boston Boston Celtics Za Darmo Gdzie Oglądać Finał Nba?"Zakłady Bukmacherskie Online, Kody Promocyjne JohnnybetContentGra T Karty W Etoto – Ciekawe Opcje Obstawiania...
Mostbet Tr Resmî Web Sitesinde Giriş Ve Kayıt OlmaOnline Spor Bahisleri Şirketi Ve CasinoContentAndroid Ve Ios Için Mostbet UygulamasıMostbet’in Başlıca AvantajlarıMostbet Com Müştərisini YükləyinMostbet...
Esports: Porównanie Kursów Bukmacherskich Watts Lipiec 2024Ggbet Strona Oficjalna Zakłady Bukmacherskie OnlineContent⃣ Czy Watts Można Wykorzystywać Fjeofj Bet Darmowe Spiny? Dane KontaktoweMiliardy Złotych Na...
Oferta Sts Zakłady Na Dzisiaj I Jutro, Wyniki, StatystykiZakłady Online Em Sport I E-sport Bukmacher 1ContentCo To Be Able To Jest Ggbet? Specjalna Oferta...

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here
Captcha verification failed!
CAPTCHA user score failed. Please contact us!

Most Popular

የአስፕሪን ጥቅም እና ጎንዮሽ ጉዳቶች

በቀን አንድ አስፕሪን መውሰድ ከጥቅሙ የበለጠ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ጥናቶች አመላከቱ፡፡ በቅርቡ በአሜሪካ ብቻ በተደረጉ ጥናቶች ከ40 ዓመት በላይ የሆናቸው ከአምስት ሰዎች መካከል አንዱ በየቀኑ...

የአዲስ አበባ የመንግስት ሠራተኞች የብቃት ምዘና: እውነተኛ ተሐድሶ ወይስ ሌላ የፖለቲካ ጫወታ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት ለሰራተኞቹ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናን ማጠናቀቁን ኢቢሲ ዘግቧል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ የብቃት ማረጋገጫ...

የኢትዮጵያ-ሶማሊላንድ የባሕር በር ስምምነት ፣ የብራክስ ሃገራት እና ምዕራብ አለም ሚድያ ዘገባ

ኢትዮጵያ የባህር በር ለመዘርጋት በቅርቡ ከሶማሊላንድ ጋር ስምምነት በጠ/ሚ አብይ በኩል አድርጋለች። ይህ ስምምነት አዳዲስ የንግድ መስመሮችን መክፈትና ወደ ውጭ የሚላኩ ዕድሎችን ማስፋት የሚያስችል...