የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዛሬው ዕለት ለሰራተኞቹ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናን ማጠናቀቁን ኢቢሲ ዘግቧል። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በአስተዳደሩ በኩል ያለውን አገልግሎት አሰጣጥና ውስጣዊ አሠራር ይበልጥ ለማሳደግ እንዲሁም ለሥራ ተነሳሽነትና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት ታቅዶ የተካሄደ መሆኑ ተዘግቧል።
በመሪህ ረገድ የብቃት ማረጋገጫ ፈተናው አስተዳደሩ አስተዳደራዊ ተሃድሶን ለመፍጠር የሚያስችለው ትክክለኛ እርምጃ ነው። በአስተዳደር ውስጥ የሚያጋጥሙትን የማያቋርጡ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን ሁለገብ በሆነ መንገድ ለመፍታት መዘጋጀቱን ያመለክታል ። አንካ ሚዲያ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ አስተዳደራዊ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ድርሻ ከፍተኛ መሆንን ስትዘግብ ከርማለች። በዚህም ረገድ የአስተዳደሩ እንቅስቃሴ ሊበረታታ ይገባል።
ነገር ግን ይህ እንቅስቃሴ ከብዙ አቅጣጫዎች ሲታይ እውነተኛ ተሐድሶ እያየን ነው ወይስ ሌላ የአስተዳደሩን የፖለቲካ ጫዋታ እየተመለከትን ነው? የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አይቀርም። ለምሳሌ የግምገማ መስፈርቱን በተመለከተ ግልጽ አለመሆን ፣ ስለ ሂደቱ ግልፅነት ትክክለኛ ጥያቄዎችን ያስነሳል። ግቡ የሚደነቅ ቢሆንም እውነተኛ አስተዳደራዊ ለውጥ ከምንም በላይ ግልጽነትን ይጠይቃል ። አስተዳደሩ በህዝቡ ዘንዳ አመኔታን ለማስፈን አስቦ የነደፈው ይህ እንቅስቃሴ ሳይታወቅ እንዳይሸረሸረው ጥንቃቄ መደረግ ያለበት መሆኑ ግልጽ ነው።
የብቃት ማረጋገጫ ፈተናው ከ15,000 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች መውሰዳቸውን ዘገባው አስፍሯል፤ ይህም አዋጭነቱ በትንሽ ያልተሞከረ አሰራር፣ ሳይሳካ ከቀረ ሊያስከትል የሚችለው የገንዘብ ብክነት የሚካድ አይደለም። አስተዳደሩ ያሉትን የሰው ሃይል ክህሎት ለማሻሻል ያደረገው ልባዊ ጥረት ሳይሆን ከጥራት ይልቅ ቁጥር ላይ ያለውን ትኩረት የሚያሳይ እንዳይሆን ያሰጋል።
የከንቲባው ቢሮ ከብቃት ማረጋገጫውም ባሻገር ቴክኖሎጂ መር አገልግሎቶችን ለመስጠት እየተዘጋጀ ሲሆን ፣ የገንዘብ ብክነትንና እንግልትን እንደሚያስቀር ቃል ገብቷል ። የአገልግሎት ብቃቱን ለማሻሻልም የተመረጡ የአስተዳደሩን ተግዳሮቶች ለሶስተኛ ወገን በመስጠት ቀልጣፋ እና ተደራሽ ግልጋሎትን ለመዘርጋት ማቀዱን አስታውቋል። ይህ ሁሉ የእንቅስቃሴ ዕቅድ በወረቀት ላይ ጥሩ ድምጽ ያለው ቢሆንም ሁለት ስለት ያለው ሰይፍ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። የሲቪል አገልግሎቶችን ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የሥራ ደህንነት ላይ እና የአገልግሎት ተጠያቂነት ላይ ያለው አሉታዊ ተጽዕኖ ሊጠና የሚገባ ነው።
የዚህ ሁሉ ለውጦች የመጨረሻ ግብ ሌብነት እና ብልሹ አሰራሮችን ለመዋጋት መሆኑ የሚደነቅ ነው። ይሁን እንጂ ሌቦቹ ራሳቸው የደገሱት እና መንስኤውን ለይቶ በቀዶ ጥገና ከማከም ይልቅ እኚን የተለመዱ ቃላቶችን በሚዲያ በመወርወር እድሜን የማራዘም ታክቲክ አለመሆኑን በውጤት ማሳየት አስፈላጊ ነው።